am_tn/luk/15/17.md

2.0 KiB

ወደ ልቡ ተመለሰ

የዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም፣ ከፍ ያለ ስህተት እንደፈጸመ እና እውነታው ምን እንደነበረ አስተዋለ፡፡ "በግልጽ ሁኔታውን ተረዳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ያህሉ የአባቴ ተቀጣሪ ሰራተኞች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ምግብ ያገኛሉ

ይህ የማጋነኑ አንዱ ክፍል ነው፤ እናም ጥያቄ አልነበረም፡፡ "የአባቴ አጋልጋዮች ሁሉ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ምግብ አላቸው"

ከረሃብ የተነሳ መሞት

ይህ ምናልባት ማጋነን አይደለም፡፡ ወጣቱ ሰው በእርግጥም ተረቧል፡፡

በሰማይ ፊት በደልኩ

የአይሁድ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ "እግዚአብሔር" የሚለውን ቃል "ሰማይ" በሚል ተክተው ይጠቀማሉ፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት በደልኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም

"ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ልጄ ብለህ ልትጠራኝ አይገባኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከተቀጣሪ ሰራተኞችህ አንዱ አድርገኝ

"እንደ አንድ አገልጋይህ ቅጠረኝ" ወይም "ቅጠረኝ እኔም ከሰራተኞችህ እንደ አንዱ እሆናለሁ፡፡" ይህ ጥያቄ ነው፤ ትዕዛዝ አይደለም፡፡ በዩቢዲ ውስጥ እንደሚገኘው "እባክህ" የሚለው ቢጨመር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡