am_tn/luk/15/15.md

1.2 KiB

እርሱ ሄደ

"እርሱ" የሚለው ቃል ታናሹን ልጅ ያመለክታል፡፡

ለ…ራሱን ተቀጣሪ አደረገ

"ከ…ዘንድ ሥራ ያዘ" ወይም "ለ…መሥራት/ማገልግል ጀመረ"

ከዚያ አገር ነዋሪዎች መሃል አንዱ

"የዚያ አገር ሰው"

አሳሞችን ለመመገብ

"ለሰውየው አሳሞች ምግብ ለመስጠት"

ደስ ብሎት በተመገበ ነበር/ሊያገኝ ተመኘ

"አግኝቶ ሊበላ በጣም ይፈልግ ነበር፡፡" ይህ የሆነው በመራቡ ምክንያት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ቢያገኝ በደስታ እስኪመገብ ድረስ በጣም ተርቦ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰብል ግልፋፊ

እነዚህ ዐሰር ናቸው፡፡ "የባቄላ ግልፋፊ" ወይም "የባቄላ/በቆሎ ልባስ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ያልታወቀውን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)