am_tn/luk/15/11.md

1.1 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ሌላ ግብረገባዊ ምሳሌ መናገር ጀመረ፡፡ ይህም አባቱን ከሚደርሰው ውርስ ድርሻውን ስለጠየቀው ወጣት ነው፡፡ (ግብረገባዊ ምሳሌ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው

ይህ አዲስ ገጸባህሪን በግብረገባዊ ምዋሌው ውስጥ ያስተዋውቃል፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች "አንድ ሰው ነበረ" ብለው ይጀምራሉ፡፡ (አዲስ እና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ስጠኝ/አምጣ

ልጁ አባቱ ወዲያውኑ ድርሻውን እንዲሰጠው ፈልጓል፡፡ ወዲያውኒ ሊደረግ የሚፈልገውን በትዕዛዝ መልክ መግለጽ የሚችል ቃል በቋንቋ ካለ ያንን መልክ መጠቀም አለባችሁ፡፡

ለእኔ የሚደርሰኝን የሀብት መጠን

"በምትሞትበት ጊዜ ልታወርሰኝ ያቀድከውን የሀብት መጠን"

በእነርሱ መሃል

"በሁለቱ ልጆቹ መሃል"