am_tn/luk/15/08.md

1.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ሌላ ግብረገባዊ ምሳሌ መናገር ይጀምራል፡፡ ይህኛው 10 የብር ሳንቲሞች ስላላት ሴት ነው፡፡

ወይም የትኛዋ ሴት…ሻማ ለኩሳ… እስክታገኘው ደረስ ተግታ አትፈልግም?

ኢየሱስ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ሰዎቹ የብር ሳንቲም ቢጠፋባቸው፣ ያንን በእርግጥ በትጋት እንደሚፈልጉ ለማስታወስ ነው፡፡ "የትኛዋም ሴት…በእርግጥ ፋኖስ ትለኩሳለች… እናም እስክታገኘው ድረስ በትጋት የጠፋባትን ትፈልጋለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ባታገኘው

ይህ መላምታዊ ሁኔታ እንጂ በዕውን ስላለች አንዲት ሴት የሚናገር ታሪክ አይደለም፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች ይህን የሚያሳዩበት መንገድ አላቸው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደዚሁም

"በተመሳሳይ መንገድ" ወይም "ሰዎች ከሴቲቱ ጋር ደስ እንደሚላቸው" ንስሃ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ "አንድ ኃጢአተኛ ንስሃ በሚገባበት ጊዜ"