am_tn/luk/14/34.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ የተሰበሰበውን ህዘውብ ማስተማሩን አጠናቀቀ፡፡

ጨው መልካም ነው

"ጨው ጠቃሚ ነው፡፡" ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሊሆኑ ለሚፈልጉ ትምህርት እየሰጠ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንዴት ዳግም ጣዕሙን ሊያገኝ ይችላል?

ኢየሱስ ይህን ጥያቄ የተጠቀመው የተሰበሰበውን ሕዝብ ለማስተማር ነው፡፡ "ዳግም ጣዕም ሊሰጠው አይችልም፡፡" ወይም "ማንም ዳግም ጣዕም ሊሰጠው አይችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የፍግ ክምር

ሰዎች አትክልት ስፍራዎችን እና እርሻን ለማልማት ማዳበሪያ ይጠቀማሉ፡፡ ጣዕም የሌለው ጨው አንዳች ጥቅም የለውም፤ ከፍግ ጋር ለመደባለቅ እንኳን አይጠቅምም፡፡ "የማዳበሪያ ቁልል" ወይም "ማዳበሪያ/ፍግ"

ወደ ውጭ ይጣላል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገል ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወደ ውጭ ይጥሉታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚሰማ ጆሮ ያለው እርሱ ይስማ

በአንዳንድ ቋንቋዎች ሁለተኛ መደብን መጠቀም ይበልጥ ተፈጥሯዊ ሊሆን ይችላል፡፡ "እናንተ መስሚያ ጆሮ ያላችሁ ስሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚሰማ ጆሮ ያለው እርሱ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "እያንዳንዱ" ጤናማ ጆሮ እስካላቸው ድረስ፣ ወይም 2) "የመረዳት ችሎታ ያለው ሁሉ፣" እግዚአብሔርን ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑትን ያሚያመለክት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይስማ

"እርሱ በሚገባ መስማት አለበት" ወይም "እርሱ እኔ ለምናገረው ትኩረት መስጠት አለበት"