am_tn/luk/14/31.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ ደቀመዝሙር ለመሆን የሚጠይቀውን ዋጋ ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ማብራራቱን ቀጥሏል፡፡

ወይም

ኢየሱስ ይህን ቃል የተጠቀመው ሰዎች አንድ ውሳኔ ከማድረጋቸው አስቀድሞ ውሳኔው የሚጠይቀውን ዋጋ ሌላ ሁኔታ ለማስተዋወቅ ነው፡፡

አስቀድሞ የማይቀመጥ እና… ከሰዎቹ/አማካሪዎቹ ምክር የማይቀበል… የቱ ንጉሥ ነው?

ኢየሱስ የተሰበሰበውብ ሕዝብ ዋጋ ስለመተመን ለማስተማር ሌላ ጥያቄ ያነሳል፡፡ " አንድ ንጉሥ… በመጀመሪያ ተቀምጦ… ከአማካሪዎቹ ምክር እንደሚቀበል ታውቃላችሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ምክር ይቀበላል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1)"በጥንቃቄ ማሰብ" ወይም 2) "አማካሪዎቹን መስማት"

አስር ሺህ…ሃያ ሺህ

"10,000…20,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ካልሆነ

ተጨማሪ መረጃዎችን መግለጽ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "ሌላውን ንጉሥ ለማሸነፍ እንደማይችል ከተገነዘበ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰላም ሁኔታዎች

"ጦርነቱን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ" ወይም "ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ሌላው ንጉሥ እርሱ እንዲያደርግ የሚፈልገው"

ከእናንተ መሃል ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው የእኔ ደቀመዝሙር መሆን አይችልም

ይህ በአዎንታዊ ግሶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያላችሁን ሁሉ የምትተዉ ብቻ ደቀመዝሙሬ መሆን ትችላላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ አሉታ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለውን ሁሉ የሚተው

"ያለውን ሁሉ ከኋላው የሚጥል"