am_tn/luk/14/25.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ይጓዝ የነበረውን የተሰበሰበውን ሕዝብ ማስተማር ጀምሯል፡፡

ማንም ወደ እኔ መጥቶ የራሱን አባት ባይጠላ … የእኔ ደቀመዝሙር ሊሆን አይችልም

እዚህ ስፍራ "መጥላት" የሚለው ሰዎች ሌለውን አስበልጠው ለኢየሱስ ለሚያሳዩት አነስ ያለ ፍቅር በግነት የቀረበ አገላለጽ ነው፡፡ "ማንም ወደ እኔ መጥቶ አባቱን ከሚወደው በላይ እኔን ካልወደደ…እርሱ የእኔ ደቀመዝሙር መሆን አይችልም" ወይም "አንድ ሰው አባቱን ከሚወደው በላይ እኔን መውደድ ከቻለ ብቻ …እርሱ የእኔ ደቀመዝሙር መሆን ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት እንደዚሁም ጥንድ አሉታ የሚሉትን ይመልከቱ)

የራሱን መስቀል የማይችል እና ከእኔ ኋላ የማይመጣ ደቀመዝሙሬ ሊሆን አይችልም

ይህ በአዎንታዊ ግሶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማንም የእኔ ደቀመዝሙር መሆን ቢፈልግ፣ የራሱን መስቀል ሊሸከም እና ሊከተለኝ ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ አሉታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የራሱን መስቀል ተሸክሞ

ኢየሱስ እያንዳንዱ ክርስቲያን መሰቀል አለበት ማለቱ አይደለም፡፡ ሮማውያን ብዙውን ጊዜ ለሮም ያላቸውን ታማኝነት እንዲያሳዩ ወንጀለኛ ሰዎች ራሳቸው የሚሰቀሉበትን መስቀል እንዲሸከሙ ያደርጉ ነበር፡፡ የዚህ ዘይቤ ትርጉም እነርሱም ለእግዚአብሔር መገዛት እና የኢየሱስ ደቀመዝሙር ለመሆን መከራ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን እንደሚገባቸው ያሳያል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)