am_tn/luk/14/18.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ግብረገባዊ ምሳሌውን መናገሩን ቀጠለ፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

የተጋበዙት ሰዎች ሁሉ ለአገልጋዩ ወደ ግብዣው ሊመጡ የማይችሉባቸውን ምክንጠቶች ሰጡ፡፡

ምክንያት መስጠት/ማቅረብ

"ወደ እራት መምጣት ያልቻሉበትን መናገር"

የመጀመሪያው እንዲህ አለው… ሌላው እንዲህ አለ… ሌላው ሰው እንዲህ አለ

አንባቢያን፣ እነዚህ ሰዎች በቀጥታ ጌታቸው ለላከው አገልጋይ እንደተናገሩ መገንዘብ መቻል ይኖርባቸዋል (ሉቃስ 14፡17) ፡፡ "የመጀመሪያው እንዲህ ሲል መልዕክት ላከ…ሌላው እንዲህ ሲል መልዕክት ላከ… ሌላውም ሰው እንዲህ ሲል መልዕክት ላከ" ወይም "የመጀመሪያው አገላጋዩ እንዲህ እንዲል ነገረው…ሌላኛው አገልጋዩ እንዲህ እንዲል ነገረው… ሌላው ሰው አገልጋዩ እንዲህ እንዲል ነገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እባክህ ይቅር በለኝ

"እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ" ወይም "እባክህን ይቅርታዬን ተቀበል"

አምስት ጥማድ በሬ

በሬዎች የእርሻ መሳሪያ ለመሳብ/ለማረስ በጥንድ ይጠመዳሉ፡፡ "10 በሬዎች በእርሻዬ ላይ ተጠምደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሙሽራ ነኝ

በቋንቋችሁ የተለመደውን አገላለጽ ተጠቀሙ፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች "አግብቻለሁ" ወይም "ሚስት ወስጃለሁ" ሊሉ ይችላሉ፡፡