am_tn/luk/14/15.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በማዕድ ከተቀመጡት መሃል አንዱ ከኢየሱስ ጋር ተነጋገረ እናም ኢየሱስ ለእርሱ በግብረገባዊ ምሳሌ ምላሽ ሰጠው፡፡ (ግብረገባዊ ምሳሌ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነርሱ መሃል በማዕድ ከተቀመጡት አንዱ

ይህ አዲስ የሆነ አንድ ሰውን ያስተዋውቃል፡፡ (አዲስ እና ነበር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ የተባረከ ነው

ሰውየው ስለ አንድ የተለየ ሰው እየተናገረ አይደለም፡፡ "እርሱ የተባረከ ነው" ወይም "ይህ ለእያንዳንዱ እንዴት መልካም ነው"

ከዚህ እንጀራ የሚበላ እርሱ

"እንጀራ" የሚለው ቃል የዋለው በአጠቃሌ መዕዱን ለማመልከተ ነው፡፡ "ከዚህ ማዕድ የሚበላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለው

ኢየሱስ ግብረ ገባዊ ምሳሌ መናገር ጀመረ፡፡ (ግብረ ገባዊ ምሳሌ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው ትልቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙዎችን ጋበዘ

አንባቢው ምናልባት የዚያ ሰው አገልጋዮች መዕደስ እንዳዘጋጁ እና እንግዶችን እንደጋበዙ መገመት መቻል ይኖርበታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው

ይህ ሀረግ ስለማንነቱ ምንም መረጃ ስላልሰጠ ሰው ማጣቀሻ መንገድ ነው፡፡

ብዙዎችን ግብዣ ጠራ

"ብዙ ሰዎች ጋበዘ" ወይም "ብዙ እንግዶች ጠራ"