am_tn/luk/14/12.md

1.3 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት መናገሩን ቀጥሏል፤ ነገር ግን የሚናገረው በቀጥታ ለጋባዡ ነበር፡፡

እርሱ የጋበዘው ሰው

"ቤቱ ግብዣ የጠራውን ፈሪሳዊ"

አንተ ስትሰጥ

"አንተ" የሚለው ነጠላ ቁጥር ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በቀጥታ የሚናገረው ለጋበዘው ፈሪሳዊ ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

አትጥራ/አተጋብዝ

ይህ ምናልባት እነዚህን ሰዎች ፈጽሞ መጋበዝ አይችሉም ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ሌሎችንም/ድሆችንም ደግሞ መጋበዝ ነበረባቸው ማለት ይመስላል፡፡ "…ብቻ አትጋብዝ" ወይም "ሁሌም…ብቻ አትጋብዝ"

ምናልባት እነርሱ

"ምክንያቱም እነርሱ"

በተራቸው ይጋብዙሃል

"ወደ እራት ወይም ግብዣ ይጠሩሃል"

መልሶ ይከፍልሃል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በዚህ መንገድ መልሰው ይከፍሉሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)