am_tn/luk/14/07.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ምሳ በጋበዘው ፈሪሳዊው ቤት ከነበሩ እንግዶች ጋር መናገሩን ቀጠለ፡፡

ተጋብዘው የነበሩ

እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ እና ይህን በአድራጊ ዐረፍተ ነገር መግለጹ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ "ከፈሪሳዊያን አለቆች አንዱ ወደ ግብዣ የጠራቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የክብር ወንበር

"ለተከበሩ ሰዎች የተዘጋጀ ወንበር" ወይም "ከፍ ላሉ ሰዎች የተዘጋጁ ወንበሮች"

አንድ ሰው በሚጋብዝህ ወቅት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው በሚጋብዝህ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በ…ጊዜ….ከዚያ አንተ…አንተን ይልሃል….አንተን ልቀቅ

በእነዚህ ስፍራዎች "አንተ" የሚሉት ተውላጠ ስሞች ነጠላ ቁጥር ናቸው፡፡ ኢየሱስ በዚያ የተሰበሰቡትን የሚያናግራቸው እያንዳንዳቸውን በግለሰብ ደረጃ እንደሚናገር አድርጎ ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ሰው ተጠርቶ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ምናልባት ደጋሹ ከአንተ ይልቅ የተከበረ ሰው ጋብዦ ሊሆን ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁለታችሁም

በዚህ ስፍራ "እናንተ" የሚለው የሚያመለክተው አንድን የክብር ስፍራ የሚፈልጉ ሁለት ሰዎችን ነው፡፡

በፍርሃት

"ታፍራለህ ደግሞም"