am_tn/luk/13/34.md

3.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ለፈሪሳውያን ምላሽ መስጠቱን አበቃ፡፡ ይህ የዚህኛው ታረክ ክፍል መጨረሻ ነው፡፡

ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም

ኢየሱስ የኢየሩሳሌም ሰዎች በዚያ ሆነው እንደሚሰደሙት አድርጎ ይናገራል፡፡ ኢየሱስ ይህን ሁለት ጊዜ የደገመው ለእነርሱ ምን ያህል እንዳዘነ ለማሳየት ነው፡፡ (ቃለ አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቢያትን የገደልሽ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የወገርሽ

ከተማን መናገር እንግዳ ነገር ከሆነ፣ ኢየሱስ በከተማይቱ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን እየተናገረ እንደሆነ ገልጽ ማድረግ ትችላላችሁ፡ "እናንተ ነቢያትን የገደላችሁ እና ወደ እናንተ የተላኩትን በድንጋይ የወገራችሁ ህዝቦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እናንተ የተላኩትን

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ወደ እናንተ የላካቸውን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ያህል አብዝቼ ፈለግሁ

"እኔ እጅግ አብዝቼ ፈለግሁ፡፡" ይህ ጉልህ ማድረግ እንጂ ጥያቄ አይደለም፡፡

ልጆችሽን ለመሰብሰብ

የኢየሩሳሌም ሰዎች የተገለጹት የእርሷ "ልጆች" ተደርገው ነው፡፡ "የአንቺን ሕዝብ ለመሰብሰብ" ወይም "የእየሩሳሉምን ሰዎች ለመሰብሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ ስር እንደምትሰበስብ

ይህ የሚገልጸው ዶሮ እንዴት ጫጬቶቿን በክንፎችዋ ሸፍና ከጥፋት እንደምትጠብቅ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቤታችሁ ወና ሆኖል

ይህ ወደፊት በቶሎ ለሚሆን ነገር ትንቢት ነው፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ሰዎች መጠበቁን አቁሟል፣ ስለዚህም ጠላት ሊያጠቃቸው እና ሊያባርራቸው ይችላል ማለት ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር እነርሱን ይበትናቸዋል፡፡ "እግዚአብሔር ይተዋችኋል" ወይም 2) ከተማቸው ባዶ ትሆናለች፡፡ "ቤታችሁ ወና ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ እስክትሉ ድረስ እኔን አታዩኝም

"እንዲህ የምትሉበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ እኔን አታዩኝም" ወይም "በሚቀጥለው ጊዜ እኔን ስታዩ፣ እንዲህ ትላላችሁ"

የጌታ ስም

እዚህ ስፍራ "ስም" የሚለው የሚያመለክተው የጌታን ሀይል እና ስልጣን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)