am_tn/luk/13/31.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ በዚህ የታሪክ ክፍል ቀጣዩ ትዕይንት ነው፡፡ አንዳንድ ፈሪሳውያን ስለ ሄሮድስ ቢነግሩትም ኢየሱስ ግን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ላይ ነው፡፡

ከዚያም ብዙ ሳይቆይ

"ኢየሱስ ንግግሩን እንደጨረሰ ወዲያውኑ"

ከዚህ በቶሎ ሂድ ምክንየቱም ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋል

ይህንን ለኢየሱስ እንደ ተሰጠ ማስጠንቀቅያ ተርጉሙት፡፡ ወደ አንድ ስፍራ እንዲሄድ እና ራሱን እንዲያድን እየመከሩት ነበር፡፡

ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋል

ሄሮድስ ሰዎች ኢየሱስን እንዲገድሉት ያዛል፡፡ "ሄሮድስ አንተን እንዲገድሉ ወታደሮቹን መላክ ይፈልጋል"

ያ ቀበሮ

ኢየሱስ ሄሮድስን ቀበሮ ብሎ እየጠራው ነበር፡፡ ቀበሮ ትንሽ የሆነ የዱር ውሻ ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሄሮድስ በፍጹም የሚያስፈራው አልነበረም 2) ሄሮድስ አሳሳች ነበር፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በማናቸውም ሁኔታ

"የሆነ ሆኖ" ወይም "ሆኖም" ወይም "የሆነው ቢሆንም"

ነቢይን ከኢየሩሳሌም ውጭ መግደል ተቀባይነት የለውም

የአይሁድ መሪዎች እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን አባቶቻቸው ብዙ የእግዚአብሔርን ነቢያት በኢየሩሳሌም ውስጥ ገድለዋል፣ እናም ኢየሱስ እርሱንም በዚህ እንደሚገድሉት ያውቃል፡፡ "የአይሁድ መሪዎች የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች የገደሉት እዚህ ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምጸት የሚለውን ይመልከቱ)