am_tn/luk/13/28.md

2.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ስለ መግባት መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ይህ የዚህ ንግግር መጨረሻ ነው፡፡

ለቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት

እነዚህ ድርጊቶች ታላቅ ጸጸትን እና ሀዘንን የሚያመለክቱ ትዕምርታዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ "ከታላቅ ጸጸታቸው የተነሳ የተከተለ ለቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

በምትመለከቱበት ጊዜ

ኢየሱስ ለተሰበሰበው ሕዝብ ወደ ሰማዩ መንግስት እንደማይገቡ አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ነገር ግን ወደ ውጭ ትጣላላችሁ

"ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ ወደ ውጭ ትጣላላችሁ፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ውጭ ይጥላችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ደቡብ

ይህ ማለት "ከሁሉም አቅጣጫ፡፡" ማለት ነው፡፡

በእግዚአብሔር መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ

የእግዚአብሔርን መንግሥት ደስታ እንደ ግብዣ መግለጽ የተለመደ ነበር፡፡ "በእግዚአብሔር መንግሥት ይጋበዛሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የመጀመሪያ ይሆናሉ…የመጨረሻ ይሆናሉ

የመጀመሪያ መሆን የሚወክለው አስፈላጊ ወይም የተከበረ መሆንን ነው፡፡ "እጅግ አስፈላጊ ይሆናሉ…የመጨረሻዎቹ ይሆናሉ" ወይም "እግዚአብሔር ያከብራቸዋል…እግዚአብሔር ያሳፍራቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)