am_tn/luk/13/22.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ለጥያቄው ምላሽ የሰጠው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ስለ መግባት ዘይቤያዊ አገላለጽ በመጠቀም ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሚድኑ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር የሚያድነው ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነውን?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በጠባቡ በር ለመግባት ታገሉ

"በጠባቡ በር ለመግባት ትጉ፡፡" ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ስለ መግባት የሚናገረው፣ ወደ ቤት እንደሚያስገባ ትንሽ በር አድርጎ ነው፡፡ ኢየሱስ ለሰዎች ስብስብ እንደመናገሩ በዚህ ትእዛዝ ውስጥ "እናንተ" የሚለው ተውላጠ ስም ብዙ ቁጥር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አንተ የሚለው ተውላተ ስም መልኮች የሚለውን ይመልከቱ)

ጠባቢቱ በር

በሩ ጠባብ መሆኑ የሚያመለክተው በውስጡ ማለፍ አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ውስንነት በሚያሳይ መንገድ ተርጉሙት፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙዎች ሊገቡባት ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ሊገቡ አይችሉም

ለመግባት ከባድ ከመሆኑ የተነሳ፣ መግባት እንደማይችሉ ተጠቁሟል፡፡ ቀጣዩ ሀረግ ከባድነቱን ያብራራል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)