am_tn/luk/13/18.md

1.4 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢየሱስ በምኩራብ ለነበሩ ሰዎች ግብረገባዊ ምሳሌ መናገር ጀመረ፡፡ (ግብረገባዊ ምሳሌ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ትመስላለች…ከምንስ ጋር አወዳድራታለሁ?

ኢየሱስ ሁለትን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው ሊያስተምር ያለውን ነገር ለማስተዋወቅ ነው፡፡ "የእግዚአብሔር መንግሥት ምን እንደምትመስል እነግራችኋለሁ…ከምን ጋር ላነጻጽራት እችላለሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምን ጋር ላነጻጽራት እችላለሁ?

ይህ ከቀደመው ጥያቄ ጋር በመሰረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች ሁለቱንም ጥያቄዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አንዱን ጥያቄ ብቻ ይጠቀማሉ፡፡(ትይዩ ንጽጽራዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ልክ እንደ ሰናፍጭ ፍሬ ናት

ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከሰነፍጭ ጋር ያነጻጽራል፡፡ "የእግዚአብሔር መንግሥት የሰናፍጭን ፍሬ ትመስላለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)