am_tn/luk/13/01.md

3.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ እስከ አሁን ድረስ ለተሰበሰበው ሕዝብ እየተናገረ ነው፡፡ ከተሰበሰበው ህስብ መሃል አንዳንዱ እርሱን ስጠይቀው እርሱም ምላሽ መስጠት ጀመረ፡፡ ይህ በሉቃስ 12፡1 ላይ የጀመረውን ታሪክ ይቀጥላል፡፡

በዚያን ጊዜ

ይህ ሀረግ፣ ኢየሱስ የተሰበሰበውን ሕዝብ በሚያስተምርበት ወቅት እሰከ ምዕራፍ 12 መጨረሻ ድረስ ያለውን ትዕይንት ያያይዛል፡፡

ጲላጦስ መስዋዕታቸውን ከደም ጋር የቀላቀላባቸው

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚያመለክተው የገሊላ ሰዎችን ሞት ነው፡፡ ምናልባት እነርሱ የተገደሉት መስዋዕታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ በዩዲቢ ውስጥ እንደቀረበው ብልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጲላጦስ መስዋዕታቸውን ከደም ጋር የቀላቀላባቸው

ምናልባት ጲላጦስ ህዝቡን የገደለው ራሱ ሳይሆን ወታደሮችን ልኮ ሊሆን ይችላል፡፡ "እንስሳትን መስዋዕት በማቅረብ ላይ እያሉ የጲላጦስ ወታደሮች የገደሏቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ የገሊላ ሰዎች በ…መንገድ ይበልጥ ኃጢአተኞች ስለሆኑ ይመስላችኋል? አይደለም፣ እኔ እላችኋለሁ

"እነዚህ ገሊላውያን ይበልጥ በ…መንገድ ኃጢአተኞች ነበሩን? አይደለም፣ እኔ እላችኋለሁ" ወይም "ይህ እነዚህ ገሊላውያን ይበልጥ በ…መንገድ ኃጢአተኞች እንደሆኑ ያረጋግጣልን? አይደለም፣ እኔ እላችኋለሁ" ኢየሱስ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት የህዝቡን መረዳት ለመገዳደር ነው፡፡ "እናንተ እነዚህ ገሊላውያን በ…መንገድ ይበልጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ ታስባላችሁ ነገር ግን አልነበሩም" ወይም "እነዚህ ገሊላውያን በ…መንገድ ይበልጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አታስቡ" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አይደለም፣ እኔ እላችኋለሁ

እዚህ ስፍራ "እኔ እላችኋለሁ" የሚለው ትኩረት የሚሰጠው "አይደለም" የሚለውን ነው፡፡ "በእርግጥ እነርሱ ይበልጥ ኃጢአተኞች አልነበሩም" ወይም "መከራ ስለደረሰባቸው ይህ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆናቸው ያረጋግጣል ብላችሁ ማሰባችሁ ስህተት ነው"

ሁላችሁም በተመሳሳይ መንገድ ትጠፋላችሁ

"ሁላችሁም ደግሞ ትሞታላችሁ፡፡" "በተመሳሳይ መንገድ" የሚለው ሀረግ ተመሳሳይ ነገር ይደርስባቸዋል ማለት እንጂ በተመሳሳይ መልክ ይሞታሉ ማለት አይደለም፡፡

መጥፋት

መሞት