am_tn/luk/12/45.md

2.5 KiB

ያ አገልጋይ

ይህ የሚያመለክተው ጌታው በሌሎች አገልጋዮች ላይ ሀላፊ ያደረገውን አገላጋይ ነው

በልቡ እንዲህ ይላል

እዚህ ስፍራ "ልብ" ለአንድ ሰው አስተሳሰብ ወይም ውስጣዊ ማንነት ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ "በውስጡ እንዲህ ብሎ ቢያስብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የጌታዬ መመለስ ይዘገያል

"አለቃዬ በቶሎ አይመለስም"

ወንድ እና ሴቶች አገልጋዮች

እዚህ ስፍራ "ወንድ እና ሴቶች አገልጋዮች" ተብለው የተተረጎሙት ቃላት "ወንድ ልጆች" እና "ልጃገረዶች" ተብለው ተተርጉመዋል፡፡ ይህ አገልጋዮቹ ወጣቶች እንደነበሩ ወይም በጌታቸው ዘንድ ተወዳጆች እንደነበሩ ሊያመለክት ይችላል፡፡

እርሱ ባልጠበቃት ቀን፣ ደግሞም እርሱ በማያውቃት ሰዓት

"ቀን" እና "ሰዓት" ከእስከ ያለውን ማናቸውንም ጊዜ ሲያመለክት፣ "በስተቀር" እና "ያውቃል" የሚሉት ቃላትም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ስለዚህም እዚህ ስፍራ ሁለቱ ሀረጎች፣ ለአገላጋዮቹ የጌታቸው መምጣት ፍጹም በድንገት እንደሚሆን ትኩረት ለመስጠት በንጽጽር የቀረቡ ናቸው፡፡ ሆኖም፣ የእናተ ቋንቋ "ማወቅ" እና "መጠባበቅ" ወይም "ቀን" እና "ሰዓት" ለሚሉት ቃላት ልዩነት የሌለው ካልሆነ በስተቀር ሀረጋቱ በአንድነት ተጣምረው መቅረብ የለባቸውም፡፡ "አገልያዩ እርሱን በማይጠባበቅበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ከጽንፍ ጽንፍ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ይቆራርጠዋል ስፍራውንም ታማኝ ካልሆኑት ጋር ያደርጋል

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ጌታው በአገልጋዩ ላይ የሚያደርሰው ከባድ ቅጣት ተጋኖ የተገለጸበት ነው፣ ወይም 2) ይህ አገልጋዩ የሚደርስበት የቅጣት ሁኔታ የሚገደል እና የሚቀበር መሆኑን ይገልጻል፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉት ይመልከቱ)