am_tn/luk/12/37.md

1.1 KiB

የተባረኩ ናቸው

"እንዴት ለእነርሱ መልካም ይሆናል"

ጌታቸው ሲመጣ እርሱን ሲጠብቁት የሚያገኛቸው

"እርሱ በሚመለስበት ጊዜ ጌታቸውን ሲጠበቁት የሚያገኛቸው" ወይም "ጌታቸው በሚመለስበት ጊዜ ዝግጁ የሆኑ"

እነርሱ ይቀመጣሉ፣ እርሱ ታጥቆ ቆሞ ያገለግላቸዋል

አገላጋዮቹ ታማኞች ስለነበሩ እና ጌታቸውን ለማገልገል ዝግጁ ስለነበሩ፣ አሁን ጌታቸው እነርሱን በማገልጋል ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል/ይሸልማቸዋል፡፡

በምሽቱ ሁለተኛ ክፍለ ጊዜ

ሁለተኛው ሰዓት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ያለው ነው፡፡ "በውድቅት ሌሊት" ወይም "ከእኩለ ለሊት አስቀድሞ"

ወይም ደግሞ በሶስተኛው ሰዓት እንኳን

ሶስተኛው ሰዓት ከእኩለሌሊት እስከ ሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ያለው ነው፡፡ "ወይም ሌሊት ዘግይቶ ቢመጣም እንኳን"