am_tn/luk/12/33.md

1.9 KiB

ለድሆች ስጡ

እነርሱ የተቀበሉትን መግለጹ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ "ከሽያጭ ካገኛችሁት ለደሆች ስጡ" (ኢሊፕሲስ- የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

ለራሳችሁ በሰማያት …ለራሳችሁ የገንዘብ ቦርሳ/ከረጢት አዘጋጁ

በሰማያት ከረጢት/የገንዘብ ቦርሳ እና ሀብት የሚሉት ተመሳሳይ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱም ነገሮች በሰማያት የእግዚአብሔርን በረከት ይወክላሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለራሳችሁ አዘጋጁ

ይህ ለድሆች በመስጠት የሚገኝ ነው፡፡ "በዚህ መንገድ ለራሳችሁ በሰማይ ታዘጋጃላችሁ"

የማይደበዝዘውን ግዙ

"ቀዳዳ የማይኖረው/የማይቀደድ የገንዘብ ቦርሳ/ ከረጢት"

ጊዜ የማያልፍበት/የማያረጅ

"የማይጠፋ" ወይም "እየመነመነ/ እያደር እያነሰ የማይሄድ"

የትኛውም ሌባ የማይቀርበው

"ሌቦች የማይደርሱበት"

የቱም ብል የማያጠፋው

"ብል የማይበላው"

ብል

"ብል" ጨርቅን እየቀደደ የሚበላ ትንሽ ነፍሳት ነው፡፡ ምናልባት እንደ ጉንዳን ወይም ምስጥ የመሰሉ ሌሎች ነፍሳትን መጠቀም ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡

ሃብታችሁ ባለበት፣ ልባችሁ በዚያ ይሆናል

"ልባችሁ ሃብታችሁ በተጠራቀመበት በዚያ ላይ ያተኩራል"

ልባችሁ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚያመለክተው የሰውን አሳተሳሰብ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)