am_tn/luk/12/27.md

1.3 KiB

ሊሊ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ

"አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ አስተውሉ"

ሊሊ አበቦች

ሊሊ አበቦች በሜዳ የሚያድጉ ውብ ተክሎች ናቸው፡፡ በቋንቋችሁ እነዚህን የአበባ አይነቶች የምትገልጹበት መንገድ ከሌለ እነዚህን አበቦች የሚመስሉ የሌሎችን አበቦች ስያሜ መጠቀም ትችላላችሁ ወይም "አበቦች" ብላችሁ መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ (የማይታወቁትን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አይፈትሉም

ክርን ወይም ፈትልን ለልብስነት ማዘጋጀት "መፍተል" ይባላል፡፡ ይህንን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "እነርሱ ልብስ ለማበጀት አይፈትሉም" ወይም "እነርሱ የስፍ ክር አያዘጋጁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰሎሞን በክብሩ ሁሉ

"ታላቅ ሀብት የነበረው፣ ሰሎሞን" ወይም "ውብ ልብሶችን የለበሰው፣ ሰሎሞን"