am_tn/luk/12/22.md

1.0 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢየሱስ በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ደቀ መዛሙርቱን ማስተማሩን ቀጠለ፡፡

ስለዚህም

"በዚህም ምክንያት" ወይም "ይህ ታሪክ ከሚያስተምረው የተነሳ"

እኔ እንዲህ እላችኋለሁ

"እኔ አስፋላጊ የሆነ ነገር ልነግራችሁ እፈልጋለሁ" ወይም "ይህንን የምነግራችሁን ነገር በጥንቃቄ ልትሰሙ ይገባል"

ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትመገቡ

"ስለ ሕይወታችሁ እና ስለምትበሉት" ወይም "ለሰውነታችሁ ስለምትለብሱት ልብስ"

ሕይወት ከመብል ስለሚበልጥ

ይህ በአጠቃላይ ስለ እሴት የሚነገር ሀሳብ ነው፡፡ "ሕይወት ከምትመገቡት ምግብ ይልቅ ይበልጥ ጠቃሚ ነው"

ሰውነት ከልብስ ይበልጣል

"ሰውነታችሁ ከምትለብሱት ልብስ ይልቅ ይበልጥ ጠቃሚ ነው"