am_tn/luk/12/20.md

1.5 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢየሱስ በምሳሌ ማስተማሩን ሲጨርስ እግዚአብሔር እንዴት ለባለጸጋው ሰው ምላሽ እንደጠቀሰ ይጠቅሳል፡፡

ዛሬ ምሽት ነፍስህ ከአንተ ትፈለጋለች

"ነፍስ" የአንድን ሰው ሕይወት ያመለክታል፡፡ "ዛሬ ምሽት ትሞታለህ" ወይም "ዛሬ ምሽት ነፍስህን ከአንተ እወስዳታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ያከማቸሃቸው ነገሮች ለማን ይሆናሉ?

"አንተ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?" ወይም "አንተ የሰበሰብከው ለማን ይሆናል?" እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ሰውየው የሰበሰባቸው ነገሮች የእርሱ እንደማይሆኑ እንዲረዳ ለማድረግ ነው፡፡ "አንተ የሰበሰብካቸው ነገሮች የሌላ ሰው ይሆናሉ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሀብት መሰብሰብ

"ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ማከማቸት"

በእግዚአብሔር ዘንድ ባለጸጋ ያልሆነ

ጊዜውን እና ሃብቱን እግዚአብሔር ዋጋ ለሚሰጣቸው ነገሮች አልተጠቀመበትም