am_tn/luk/12/13.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ በኢየሱስ ትምህርት መሃል ጣልቃ የገባ ድርጊት ነው፡፡ አንድ ሰው ኢየሱስን አንድ ነገር እንዲያደርግ ይጠይቀውል እርሱም ለሰውየው መልስ ይሰጠዋል፡፡

ከእኔ ጋር ውርስ አካፍለን

በዚያ ባህል ውስጥ፣ ብዙውን ጊዜ አባት ከሞተ በኋላ ውርስ ይተላለፋል፡፡ የተናጋሪው ሰው አባት መሞቱን ማረጋገጥ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "አሁን አባታችን ስለ ሞተ ድርሻዬን ከሀብቱ አካፍለኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ እንግዳ የሆነን ለማመልከት የሚውል ነው፤ ወይም 2) ኢየሱስ ሰውየውን እየገሰጸው ነው፡፡ የእናንተ ቋንቋ ከእነዚህ በአንዱ መንገዶች በአንዱ ሰዎችን ሊገልጽ የሚችልበት መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡ አንዳንዶች ይህን ቃል ከነጭርሱ ሳይተረጉሙት ይቀራሉ፡፡

ማን በእናንተ መሃል ዳኛ ወይም አካፋ አደረገኝ?

ኢየሱስ ጥያቄውን የተጠቀመበት ሰውየውን ለመገሰጽ ነው፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች "አንተ" ወይም "የአንተ" ለሚለው ብዙ ቁጥርን ይጠቀማሉ፡፡ "እኔ የእናንተ ዳኛ ወይም ፈራጅ አይደለሁም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእነርሱ እንደዚህ አላቸው

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው ቃል ምናልባት በዚያ የተሰበሰበውን ሕዝብ ሁሉ ሊያመለክት ይችላል፡፡ "ኢየሱስ በዚያ ለተሰበሰቡት እንዲህ አላቸው"

ከስግብግብነት ምኞት ሁሉ ራሳችሁን ጠብቁ

"ከማናቸውም አይነት ራስ ወዳድነት ተጠበቁ፡፡" "ከአፍቅሮተ ንዋይ ራሳችሁን አርቁ" ወይም "የንዋይ ፍቅር እንዳይገዛችሁ ራሳችሁን ጠብቁ"

የሰው ሕይወት

ይህ እውነታን የሚያንጸባርቅ አጠቃለይ ሀሳብ ነው፡፡ አንደን ሰው ለይቶ አያመለክትም፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች ይህን የሚገልጹበት መንገድ አላቸው፡፡

የሀብቱ ብዛት

"ምንም ያህል ሀብት ያለው መሆኑ" ወይም "የቱንም ያህል ንብረት ይኑረው"