am_tn/luk/12/08.md

2.8 KiB

እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ

ኢየሱስ ወደ አዲስ ርዕስ ለመግባት፣ በዚህ ሁኔታ ስለ ንስሃ ለማስተማር አድማጮቹን ዳግም እንዲህ ይላቸዋል፡፡

በሰዎች ፊት ስለ እኔ ለሚመሰክረው ሁሉ

የሚመሰከረው ነገር በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስለ እኔ ለሌሎች የሚመሰክር እርሱ የእኔ ደቀ መዝሙር ነው" ወይም "ለእኔ ታዛዥ መሆኑን ለመናገር አሻፈረኝ የሚል፣ እርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

ኢየሱስ የሚናገረው ስለ ራሱ ነው፡፡ "እኔ፣ የሰው ልጅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በሰዎች ፊት የሚክደኝ እርሱ

"በሰዎች ፊት የሚክደኝ እርሱ፡፡" የተደረገው ክህደት ምን እንደሆነ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "የእኔ ደቀ መዝሙር መሆኑን በሌሎች ፊት እውቅና ለምጠት ያልፈቀደ" ወይም "ለእኔ ታዛዥ መሆኑን ለመናገር ያልፈቀደ እርሱ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እክደዋለሁ

"ተቀባይነት አያገኝም፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የሰው ልጅ እርሱን ይክደዋል" ወይም "የእኔ ደቀ መዝሙር አይደለም እላለሁ/እክደዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰው ልጅ ላይ የሚናገር ሁሉ

"ስለ ሰው ልጅ ክፉ ነገር የሚናገር ሁሉ"

ይቅር ይባላል

"ይቅርታ ይቀበላል፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ይምረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ

"በመንፈስ ቅዱስ ላይ ክፉ የሚናገር"

ነገር ግን እርሱ… ይቅር አይባልለትም

ይህ በአድራጊ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ነገር ግን እርሱ… እርሱን እግዚአብሔር ይቅር አይለውም" ወይም "ነገር ግን እርሱ… እግዚአብሔር እርሱን ለዘለዓለም ጥፋተኛ ያደርገዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)