am_tn/luk/12/06.md

1.9 KiB

አምስት ድንቢጦች በሁለት ሳንቲም ይሸጡ የለምን?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ "አምስት ድንቢጦች በሁለት ሳንቲም ብቻ እንደሚሸጥ ታውቃላችሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንቢጦች

ጥራጥሬ የሚመገቡ፣ በጣም ትንንሽ ወፎች

በእግዚአብሔር ዐይኖች አንዳቸውም እንኳን አልተረሱም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር እና በአዎንታዊ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ከእነርሱ አንዲቱን አንኳን በፍጹም አይረሳም" ወይም "እግዚአብሔር በእርግጥ እያንዳንዷን ድንቢጥ እንኳን አይረሳም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እን ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

እያንዳንዲቱ የራሳችሁ ፀጉር እንኳን የተቆጠረች ናት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በራሳችሁ ላይ ስንት ፀጉር እንዳለ እንኳን ያውቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አትፍሩ

ለፍርሃቱ ምክንያት የሚሆነው ነገር አልተገለጸም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በሚደርስባችሁ ነገር አትፍሩ" ወይም 2) "ስለዚህ ሊጎዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን እትፍሩ፡፡"

እናንተ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ይበልጥ ዋጋ አላችሁ

"እናንተ ለእግዚአብሔር ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ዋጋ አላችሁ"