am_tn/luk/12/02.md

3.6 KiB

ነገር ግን በዚያ አለ

"ነገር ግን" የሚለው ቃል ስለ ፈሪሳውያን ግብዝነት ለመግለጽ ይህንን ሀረግ ከቀደመው ሀረግ ጋር ያያይዛል፡፡ (አያያዥ ቃላት የሚለውን ይመልከቱ)

ሳይገለጥ ተሸፍኖ የሚቀር ምንም ነገር የለም

"ማናቸውም የተደበቀ ነገር ይገለጣል፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች በሌሎች ሰዎች በድብቅ የተደረገን ማናቸውንም ነገር ይደርሱበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሳይታወቅ ተደብቆ የሚቀር ምንም ነገር የለም

ይህ ከዐረፍተ ነገሩ የመጀመሪያ ክፍል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ያለው እውነቱን ላይ ትኩረት የሚሰጥ አገላለጽ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች ሌሎች ሰዎች ሊደብቁ ስለሚሞክሩት ነገር በሙሉ ማወቅ ይችላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በጨለማ ውስጥ የተናገራችሁት ነገር ሁሉ በብርሃን ይሰማል

እዚህ ስፍራ "ጨለማ" የሚለው "ምሽት" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን ይህም "በግል" ለሚለው ሜቶኖሚ ነው፡፡ እንደዚሁም "ብርሃን" የሚለው "ቀን" ለሚለው ሜቶኖሚ ሲሆን ይህም "ሕዝብ" ለሚለው ሜቶኖሚ ነው፡፡ "ይሰማል" የሚለው ሀረግ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በምሽት ብቻችሁን ሆናችሁ የተናገራችሁትን፣ ሰዎች በቀን ብርሃን ይሰሙታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በጆሮ የተነገረ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ለሌላ ሰው ማንሾካሾክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጠኛው ክፍሎች/በጓዳ

"በተዘጋ ክፍል፡፡" ይህ የግል ንግግርን ያመለክታል፡፡ "በግል" ወይም "በድብቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ይሰማል

"ከፍ ባለ ድምጽ ይነገራል፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች ያሰሙታል/ይናገሩታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በቤቶች ሰገነት ላይ

በእሥራኤል ቤቶች ጠፍጣፋ ጣራ/ሰገነት አላቸው፤ ስለዚህም ሰዎች ወደዚያ ላይ ወጥተው ሊቆሙ ይችላሉ፡፡ ሰዎች እንዴት በቤት ጫፍ ላይ እንደሚወጡ ለመገመት አንባቢው ግር የሚለው ከሆነ፤ ይህ አጠቃላይ በሆነ መንገድ፣ "ሁሉም ሰው ሊሰማው በሚችለው ከፍ ባለ ስፍራ" በሚል ሊተረጎም ይችላል፡፡