am_tn/luk/11/53.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት የሚበላበት የታሪኩ የመጨረሻ ክፍል ነው። የታሪኩ ዋነኛው ክፍል ካለቀ በኋላ ስለሆነው ነገር እነዚህ ቁጥሮች ለአንባቢው ይናገራሉ።

ኢየሱስ ከዚያ ከሄደ በኋላ

“ኢየሱስ ከፈሪሳዊው ቤት ወጥቶ ከሄደ በኋላ”

ለማጥመድ በመሞከር … ከእርሱ ጋር ተከራከሩ

ጸሐፊዎችና ፈሪሳውያን ከኢየሱስ ጋር የተከራከሩት የእግዚአብሔርን ሕግ ስለ ማፍረሱ ሊከሱት እንዲችሉ ለማጥመድ በመሞከር እንጂ አመለካከታቸውን ለማስከበር አልነበረም።

በራሱ ቃል ሊያጠምዱት በመሞከር

ይህ ማለት ሊከሱት ይችሉ ዘንድ ኢየሱስ አንድ የተሳሳተ ነገር እንዲናገር ፈልገዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)