am_tn/luk/11/49.md

2.6 KiB

በዚህ ምክንያት

ይህ ቀደም ሲል የሕግ መምህራን መመሪያዎችን በሕዝቡ ላይ ስለመጫናቸው የተነገረውን መግለጫ ወደ ኋላ ያመለክታል።

የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች

“ጥበብ” ስለ እግዚአብሔር ሆና መናገር እንደቻለች ተደርጋ ተወስዳለች። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በጥበቡ እንዲህ አለ” ወይም “እግዚአብሔር በጥበብ ተናገረ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ

“ለሕዝቤ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ”። ኢየሱስ ይናገራቸው ለነበሩ አይሁድ አድማጮች፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ነቢያትንና ሐዋርያትን እንደሚልክ አስቀድሞ አስታውቋቸው ነበር።

ከእነርሱ አንዳንዶቹን ያሳድዳሉ፣ ይገድላሉም

“ሕዝቤ ከነቢያትና ከሐዋርያት አንዳንዶቹን ያሳድዳሉ፣ ይገድላሉም”። ኢየሱስ ይናገራቸው ለነበሩ አይሁድ አድማጮች እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ነቢያትንና ሐዋርያትን እንደሚያሳድዱና እንደሚገድሉ አስቀድሞ አስታውቋቸው ነበር።

እንግዲህ ለፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ይህ ትውልድ ተጠያቂ ይሆናል

ኢየሱስ ይናገራቸው የነበሩ ሰዎች በአባቶቻቸው ስለ ተገደሉት ነቢያት ተጠያቂዎች ይሆናሉ። አ.ት፡ “ስለዚህ ሰዎች ስለ ገደሏቸው ነቢያት ሞት በሙሉ እግዚአብሔር ይህንን ትውልድ ተጠያቂ ያደርገዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የፈሰሰው የነቢያት ደም

“ደም… ፈሰሰ” በተገደሉ ጊዜ የተረጨውን ደም ያመለክታል። አ.ት፡ “የነቢያትን መገደል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዘካርያስ

ይህ ምናልባት በብሉይ ኪዳን ስለ ጣዖት አምልኮአቸው የእስራኤልን ሕዝብ የገሰጻቸው ካህን ይሆን ይሆናል። ይህ የአጥማቂው ዮሐንስ አባት አይደለም።

የተገደለው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሕዝቡ የገደሉት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)