am_tn/luk/11/45.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ለአይሁዳዊው መምህር ምላሽ መስጠት ይጀምራል።

ከሕግ መምህራን አንዱ

ይህ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ገጸ ባህርይን ያስተዋውቃል። (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

በምትናገረው እኛንም መሳደብህ ነው

ኢየሱስ በፈሪሳውያን ላይ የሰጠው አስተያየት የአይሁድ የሕግ መምህራንንም የሚመለከት መስሏል።

ወዮላችሁ እናንተ የሕግ መምህራን!

ኢየሱስ ከፈሪሳውያን ጋር የሕግ መምህራኑንም ተግባር ለመኮነን መፈለጉን ግልጽ ያደርጋል።

ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሕዝብ ላይ ትጭናላችሁ

“ሊሸከሙት የማይችሉትን ከባድ ሸክም በሕዝብ ላይ ትጭናላችሁ”። ኢየሱስ የሚናገረው አንድ ሰው ከባድ ነገሮችን እንዲሸከሙት ለሕዝብ ይሰጣቸው ይመስል ብዙ መመሪያዎችን ስለሚሰጣቸው ሰው ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሸክሙን ከጣቶቻችሁ በአንዱ መንካት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ሕዝቡ እነዚያን ከባድ ሸክሞች እንዲሸከም ለመርዳት ምንም ነገር አታደርጉም” ወይም 2) “እነዚያን ሸክሞች ራሳችሁ ለመሸከም ምንም ጥረት አታደርጉም”