am_tn/luk/11/43.md

1.5 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ፈሪሳውያንን መናገሩን ያበቃል።

ከፊት ያሉ መቀመጫዎች

“ምርጥ መቀመጫዎች”

የአክብሮት ሰላምታ

“ሰዎች በልዩ አክብሮት ሰላምታ እንዲሰጧችሁ ትወዳላችሁ”

ሰዎች ሳያውቁት በላዩ ላይ እንደሚሄዱበት ምልክት የሌለበት መቃብር ናችሁ

ፈሪሳውያን ምልክት እንደሌለበት መቃብር ናቸው፣ ምክንያቱም በሃይማኖት ሥርዓት ንጹሕ ይመስላሉ፣ ነገር ግን በዙሪያቸው ያሉት እንዲረክሱ ያደርጋሉ። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)

ምልክት የሌለበት መቃብር

እነዚህ መቃብሮች አስክሬን የሚቀበርባቸው የተቆፈሩ ጉድጓዶች ናችው። እነዚህ ሌሎች ሰዎች ያዩአቸው ዘንድ እንደተለመደው ሰዎች በመቃብር ሥፍራ የሚያስቀምጧቸው ነጭ ድንጋዮች የሏቸውም።

ሳያውቁት

አይሁድ በመቃብር ላይ በሚሄዱበት ጊዜ በሃይማኖታዊው ሥርዓት ይረክሳሉ። እነዚህ ምልክት የሌለባቸው መቃብሮች በድንገት እንዲረክሱ ያደርጓቸዋል። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሳያስተውሉት እና በሃይማኖታዊ ሥርዓት እርኩስ ይሆናሉ”