am_tn/luk/11/42.md

1.8 KiB

ከአዝሙድ፣ ጤና አዳምና ከሌሎችም የጓሮ ዕጾች አሥራት ታወጣላችሁ

“ከአዝሙድ፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች የጓሮ ዕጾቻችሁ አንድ አሥረኛውን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ”። ከገቢያቸው ላይ አሥረኛውን ከመስጠት አንጻር ፈሪሳውያን እንዴት ያለ ጽንፍ እንደነበራቸው ኢየሱስ ምሳሌ እየሰጠ ነበር።

አዝሙድና ጤና አዳም

እነዚህ ዕጾች ናቸው። ሰዎች ከእነዚህ ቅጠላ ቅጠሎች ቀንጥሰው ጣዕም እንዲሰጥ ምግባቸው ላይ ይጨምራሉ። ሰዎች አዝሙድና ጤና አዳም ምን እንደሆኑ ካላወቁ እነርሱ የሚያውቁትን የዕጽ ስም ወይም “ዕጾች” የሚል ጥቅል አገላለጽ መጠቀም ትችላለህ። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

ከሌላ የጓሮ ዕጽ ሁሉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ከሌላ ከእያንዳንዱ አትክልት” 2) “ከሌላ የጓሮ ዕጽ ሁሉ” ወይም 3) “ከሌላ የጓሮ ተክል ሁሉ” የሚሉት ናቸው።

የእግዚአብሔር ፍቅር

“እግዚአብሔርን ለመውደድ” ወይም “ለእግዚአብሔር የሆነ ፍቅር”። የሚወደደው እግዚአብሔር ነው።

ሌሎቹን ነገሮች ማድረግን ደግሞ ሳትተዉ

“ሳትተዉ” ይህ ሁልጊዜ መደረግ እንዳለበት አጽንዖት ይሰጣል። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሌሎቹንም መልካም ነገሮች እንዲሁ አዘውትራችሁ ለማድረግ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)