am_tn/luk/11/39.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ዘይቤአዊ አነጋገርን በመጠቀም ለፈሪሳዊው መናገር ይጀምራል። እርሱ ሲኒና ጎድጓድ ሳህኖችን የሚያነጹበትን መንገድ ራሳቸውን ከሚያነጹበት ጋር ያነጻጽራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሲኒውንና የጎድጓድ ሳህኑን ውጫዊ ገጽ

የዕቃ መያዣዎቹን ውጫዊ ገጽ ማጠብ የፈሪሳውያን የሃማኖታዊ ሥርዓታቸው አካል ነበር።

ነገር ግን ውስጣችሁ በስስትና በክፋት የተሞላ ነው

ይህ የዘይቤአዊ አነጋገር ክፍል የሳህኑን ውጫዊ ገጽታ ለማጽዳት የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ቸል ከሚሉት ውስጣዊ ሁኔታቸው ጋር ያነጻጽራል።

እናንተ ሞኞች

እዚህ ጋ ኢየሱስ የሚናገራቸው ሁሉ ወንዶች ፈሪሳውያን ቢሆኑም እንኳን ይህ አገላለጽ ወንዶችን ወይም ሴቶችን ሊያመለክት ይችላል።

ውጪውን የሠራው እርሱ ውስጡን ደግሞ አይሠራውም?

እግዚአብሔር በውስጣቸው ስላለው ነገር እንደሚገደው ባለማስተዋላቸው ኢየሱስ ፈሪሳውያንን በጥያቄ ይገስጻቸዋል። ይህ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ውጪውን የሠራው እርሱ ውስጡንም ደግሞ ሠርቶታል!” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ

ይህ በሲኒዎቻቸውና በጎድጓዳ ሳህኖቻቸው ሊያደርጉት የሚገባቸውን ያመለክታል። አ.ት፡ “በሲኒዎቻችሁና በጎድጓዳ ሳህኖቻችሁ ውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ” ወይም “ለድኾች ለጋሾች ሁኑ”

ሁሉም ነገር ንጹሕ ይሆንላችኋል

“ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ” ወይም “በውስጣችሁና በውጪአችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ”