am_tn/luk/11/33.md

3.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ሕዝቡን ማስተማሩን ይጨርሳል።

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 33 36 ያሉት ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲታዘዙትና ከሌሎች ጋር እንዲካፈሉት ስለሚፈልገው “ብርሃን” ስለሆነው ትምህርቱ የተናገረባቸው ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በድብቅ ቦታ ወይም ከቅርጫት በታች ያስቀምጠዋል

“ይደብቀዋል ወይም ከቅርጫት በታች ያስቀምጠዋል”

ነገር ግን በመብራት ማስቀመጫ ላይ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ መገንዘብ በሚቻለው ባለቤትና ግሥ ላይ መጨመር ይቻላል። አ.ት፡ “ነገር ግን አንድ ሰው በመብራት ማስቀመጫው ላይ ያስቀምጠዋል” ወይም “ነገር ግን አንድ ሰው በጠረጴዛ ላይ ያስቀምጠዋል”

ዐይንህ የሰውነትህ መብራት ነው

በዚህ የዘይቤአዊ አነጋገር ክፍል ውስጥ ልክ ዐይን ለሰውነት ብርሃንን እንደሚያቀርብ ኢየሱስ ሲያደርግ የሚያዩአቸው ነገሮች ማስተዋልን ያቀርቡላቸዋል። አ.ት፡ “ዐይንህ ልክ እንደ ሰውነት መብራት ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዐይንህ

ዐይን የማየት ችሎታ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰውነት

ሰውነት ለሰው ሕይወት ነው።

ዐይንህ ጤነኛ በሚሆንበት ጊዜ

እዚህ ጋ፣ “ዐይን” የማየት ችሎታ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የማየት ችሎታህ ጤነኛ በሚሆንበት ጊዜ” ወይም “በሚገባ በምታይበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰውነትህ በሙሉ በብርሃን ይሞላል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰውነትህን በሙሉ ብርሃን ይሞላዋል” ወይም “ሁሉንም ነገር አጥርተህ ለማየት ትችላለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ዐይንህ በሚታመምበት ጊዜ

እዚህ ጋ፣ “ዐይን” የማየት ችሎታ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የማየት ችሎታህ በሚታወክበት ጊዜ” ወይም “በሚገባ ማየት በማትችልበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰውነትህ በጨለማ የተሞላ ነው

“ምንም ነገር ለማየት አትችልም”

በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ

“ብርሃን ነው ብለህ የምታስበው ጨለማ ሆኖ እንዳይገኝ አረጋግጥ” ወይም “የትኛው ብርሃን፣ የትኛው ደግሞ ጨለማ መሆኑን ስለ ማወቅህ እርግጠኛ ሁን”

ከዚያም ሙሉ ሰውነትህ ብርሃን ድምቀቱን በላይህ ላይ በሚያንጸባርቅበት ጊዜ የሚመስለውን ዓይነት ይሆናል

ኢየሱስ ተመሳሳዩን እውነት በተነጻጻሪ ይናገራል። እርሱ እውነትን ሰለ ተሞሉ ሰዎች በድምቀት እንደሚያበሩ መብራቶች አድርጎ ይናገርላቸዋል። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)