am_tn/luk/11/31.md

1.0 KiB

የደቡብ ንግሥት

ይህ የሳባን ንግሥት ያመለክታል። ሳባ ከእስራኤል በስተደቡብ የነበረ መንግሥት ነው።

ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር በፍርድ ትነሣለች

“ተነሥታ በዚህ ዘመን ሰዎች ላይ ትፈርዳለች”

ከምድር ጫፍ መጥታለች

ይህ የአነጋገር ዘይቤ በጣም ሩቅ ከሆነ ቦታ መጥታለች የሚል ትርጉም አለው። አ.ት፡ “በጣም ረጅም ርቀት ተጉዛ መጥታለች” ወይም “በጣም ሩቅ ከሆነ ቦታ መጥታለች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ

ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ራሱ ነው። አ.ት፡ “ከሰለሞን የምበልጠው እኔ እዚህ አለሁ”

ከሰለሞን የሚበልጥ

ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ራሱ ነው። አ.ት፡ “እኔ ከሰለሞን እበልጣለሁ”