am_tn/luk/11/24.md

1.7 KiB

ውሃ በሌለበት ሥፍራ

ይህ ክፉ መናፍስት የሚቅበዘበዙበትን “ኦና ሥፍራ” ያመለክታል።

ምንም አያገኝም

“መንፈስ በዚያ ምንም ዓይነት እረፍት በሚያጣበት ጊዜ”

ትቼው ወደ መጣሁበት ቤቴ

ይህ ለመኖሪያነት የተጠቀመበትን ሰውዬ ያመለክታል። አ.ት፡ “ወደ ኖርኩበት ሰው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ያ ቤት ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል

ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ተጠርጎ በጸዳውና ነገሮች ተስተካክለው በተቀመጡበት ቤት ስለተመሰለው ሰው ይናገራል። ቤቱ እስካሁን ድረስ ባዶ እንደሆነ ያመላክታል። ይህ ግልጽ ካደረገው መረጃ ጋር በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰውዬው ልክ አንድ ሰው ጠርጎ ያጸዳውና ሁሉንም ነገር በተገቢው ቦታ አድራጅቶ በማስቀመጥ የተወውን ቤት መስሎ ያገኘዋል” ወይም “ሰውዬው የጸዳና የተደራጀ፣ ነገር ግን የተተወ ቤት መስሎ ያገኘዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ

“መጀመሪያ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እርኩሱ መንፈስ ሳይለቀው በፊት የነበረውን የሰውዬውን ሁኔታ ነው። አ.ት፡ “መንፈሱ ሳይለቀው በፊት ከነበረው ሁኔታ ይልቅ የከፋ”