am_tn/luk/11/21.md

1.9 KiB

ብርቱ ሰው … ጊዜ የሰውዬው ንብረት

ይህ ኢየሱስ ብርቱ ሰው ሆኖ የሌላውን ብርቱ ሰው ንብረት ይወስድ ይመስል እርሱ ሰይጣንን እና አጋንንቶቹን ስለ ማሸነፉ የሚናገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የጦር መሣሪያውን ከሰውዬው ይወስድበታል

“የሰውዬውን የጦር መሣሪያና መከላከያ ያስወግዳል”

ንብረቱ ይጠበቅለታል

“ማንም የእርሱን ነገር ሊሰርቅበት አይችልም”

የሰውዬውን ሀብት ይበዘብዛል

“ሀብቱን ይሰርቀዋል” ወይም “የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ይወስዳል”

ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ይበትናል

ይህ የሚያመለክተው የትኛውንም ሰው ወይም የሰዎች ቡድን ነው። “ከእኔ ጋር ያልሆነ ማንም ቢሆን ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ማንም ቢሆን ይበትናል” ወይም “ከእኔ ጋር ያልሆኑት እነርሱ ይቃወሙኛል፣ ከእኔ ጋር የማይሰበስቡ እነዚያም ይበትናሉ”

ከእኔ ጋር ያልሆነ

“እኔን የማይደግፈኝ” ወይም “ከእኔ ጋር የማይሠራ”

ይቃወመኛል

“እኔን በመቃወም ይሠራል”

ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ይበትናል

ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ይበትናል ኢየሱስ የሚያመለክተው እርሱን የሚከተሉ ደቀ መዛሙርትን መሰብሰብን ነው። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች መጥተው እንዲከተሉኝ የማያደርግ ማንም ቢኖር ከእኔ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል”