am_tn/luk/11/18.md

2.7 KiB

ሰይጣን እርስ በእርሱ ከተከፋፈለ

እዚህ ጋ፣ “ሰይጣን” የሚያመለክተው እርሱን የሚከተሉትን አጋንንትን እንዲሁም ራሱን ሰይጣንን ነው። አ.ት፡ “ሰይጣንና በመንግሥቱ ያሉ አባላቱ እርስ በእርሳቸው ከተዋጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰይጣን … ከሆነ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል?

ኢየሱስ ሕዝቡን ለማስተማር ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰይጣን . . . ከሆነ መንግሥቱ አይጸናም” ወይም “ሰይጣን . . . መንግሥቱ ይፈራርሳል”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አጋንንትን የማወጣው በብኤልዜቡል እንደሆነ ትላላችሁና

“አጋንንትን ከሰዎች የማወጣው በብኤልዜቡል ኃይል እንደሆነ ትናገራላችሁና”። የክርክሩ ቀጣይ ክፍል በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አጋንንትን ከሰዎች የማወጣው በብኤልዜቡል ኃይል እንደሆነ ትናገራላችሁና። ያ ደግሞ ሰይጣን እርስ በእርሱ ተከፋፍሏል ማለት ነው”

ነገር ግን እኔ … ተከታዮቻችሁ በማን ያወጧቸዋል?

“ነገር ግን እኔ . . . ተከታዮቻችሁ አጋንንት ከሰዎች እንዲወጡ በማን ኃይል ያስገድዷቸዋል?” ኢየሱስ ሕዝቡን ለማስተማር ጥያቄዎችን ይጠይቃል። ኢየሱስ የሚጠይቀው ጥያቄ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ነገር ግን እኔ . . . እንግዲያውስ ተከታዮቻችሁም ደግሞ አጋንንትን የሚያወጡት በብኤልዜቡል ኃይል ነው ብለን መስማማት አለብን። ይሁን እንጂ ይህ እውነት እንደሆነ አታምኑም”።

እነርሱ ፈራጆቻችሁ ይሆናሉ

“እኔ በብኤልዜቡል ኃይል አጋንንትን እንደማወጣ ስለማለታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል አጋንንትን የሚያወጡ ተከታዮቻችሁ ይፈርዱባችኋል”

በእግዚአብሔር ጣት

“የእግዚአብሔር ጣት” የእግዚአብሔርን ኃይል ያመለክታል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንግዲያው የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች

“ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መምጣቷን ያሳያል”