am_tn/luk/11/16.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ለሕዝቡ ምላሽ መስጠት ይጀምራል።

ሌሎች ፈተኑት

“ሌሎች ሰዎች ኢየሱስን ፈተኑት”። ሥልጣኑ ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዲያረጋግጥላቸው ፈለጉበት።

ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት

“ከሰማይ ምልክት እንዲሰጣቸው ለመኑት” ወይም “ከሰማይ ምልክት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ”። ሥልጣኑ ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዲያረጋግጥላቸው የፈለጉት እንዲህ ባለ መንገድ ነበር።

እርስ በእርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል

እዚህ ጋ፣ “መንግሥት” የሚያመለክተው በውስጡ የሚኖረውን ሕዝብ ነው። ይህም ደግሞ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በአንድ መንግሥት ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች እርስ በእርሳቸው ከተዋጉ መንግሥታቸውን ያጠፋሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እርስ በእርሱ የሚከፋፈል ቤት ይወድቃል

እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “የቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ ከተጣሉ ቤተሰባቸውን ይበታትኑታል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይወድቃል

“ተሰባብሮ ይወድቅና ይጠፋል”። ይህ የሚደረመስ ቤት ስዕል የሚያመለክተው የቤተሰብ አባላት እርስ በእርስ በሚጣሉበት ጊዜ ቤተሰቡ የሚጠፋ መሆኑን ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)