am_tn/luk/11/14.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ከዲዳው ሰው አጋንንትን ካወጣ በኋላ ጥያቄ ይቀርብለታል።

በዚህ ጊዜ

ደራሲው የአዲስ ሁነት ጅማሬን ለማመልከት ይህንን ቃል ይጠቀማል። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

ኢየሱስ አጋንንትን ያስወጣ ነበር

ልዩ መረጃ መጨመር ሊረዳ ይችል ይሆናል። አ.ት፡ “ኢየሱስ ከአንድ ሰው አጋንንትን ያወጣ ነበር” ወይም “ኢየሱስ፣ አጋንንት ሰውየውን እንዲለቀው ያደርግ ነበር”

ዲዳ የሆነ አጋንንት ነበር

አጋንንቱ ሰዎችን ከመናገር የሚከለክልበት ኃይል ነበረው። አ.ት፡ “ሰውየው መናገር እንዳይችል አድርጎት የነበረው አጋንንት”

በዚህ ጊዜ

ድርጊቱ የቱ ጋ እንደሚጀምር ለማመልከት ይህ ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ ውሏል። የአንተ ቋንቋ ይህንን የሚያደርግበት መንገድ ካለው ያንን እዚህ ጋ ስለመጠቀም ማሰብ ይኖርብሃል። አጋንንቱ ከሰውዬው በወጣ ጊዜ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ኢየሱስን ነቀፉት፣ ይህም ኢየሱስ ስለ ክፉ መናፍስት ወዳስተማረው ትምህርት የሚመራ ሆነ።

አጋንንቱ በወጣ ጊዜ

ልዩ መረጃ መጨመር ሊረዳ ይችል ይሆናል። አ.ት፡ “አጋንንቱ ከሰውዬው በወጣ ጊዜ” ወይም “አጋንንቱ ሰውዬውን በለቀቀው ጊዜ”

ዲዳ የነበረው ሰው ተናገረ

“መናገር የማይችል የነበረው ሰው በዚህ ጊዜ ተናገረ”

በብኤልዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል

“አጋንንትን የሚያወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብኤልዜቡል ኃይል ነው”