am_tn/luk/11/11.md

1.5 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ስለ ጸሎት ለደቀ መዛሙርቱ ማስተማሩን ይጨርሳል።

ከእናንተ የትኛው አባት … ዓሣ?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር በጥያቄ ይጠቀማል። ይህ እንደ መግለጫ ደግሞ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “አባቶች ከሆናችሁት ከእናንተ ማንም … ዓሣ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ወይስ … ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋል?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር በጥያቄ ይጠቀማል። ይህ እንደ መግለጫ ደግሞ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “እንቁላል ቢለምናችሁ በፍጹም ጊንጥ አትሰጡትም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ጊንጥ

ጊንጥ ከሸረሪት ጋር ይመሳሰላል፣ ነገር ግን እርሱ መርዛማ መናደፊያ ጭራ አለው። አንተ ባለህበት አካባቢ ጊንጥ የማይታወቅ ከሆነ “መርዛማ ሸረሪት” ወይም “የሚናደፍ ሸረሪት” ብለህ ልትተረጉመው ትችላለህ። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

ክፉ የሆናችሁ እናንተ . . . ካወቃችሁ

“እናንተ ክፉ የሆናችሁት . . . ካወቃችሁ” ወይም “ኃጢአተኞችም እንኳን ብትሆኑ፣ እናንተ . . . ታውቃላችሁ”