am_tn/luk/11/09.md

2.0 KiB

ለምኑ … ፈልጉ … አንኳኩ

ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ባለማቋረጥ እንዲጸልዩ ለማበረታታት እነዚህን ትዕዛዞች ይሰጣቸዋል። አንዳንድ ቋንቋዎች ከእነዚህ ግሦች ጋር ተጨማሪ መረጃ ደግሞ ይፈልጉ ይሆናል። በዚህ ዐውድ በይበልጥ ተስማሚ የሚሆነውን “እናንተ” የሚለውን ቃል ተጠቀሙ። አ.ት፡ “የሚያስፈልጋችሁን መለመናችሁን ቀጥሉበት … ከእግዚአብሔር የምትፈልጉትን መፈለጋችሁን ቀጥሉ … አግኙት … በሩን ማንኳኳታችሁን ቀጥሉ”

ይሰጣችኋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እርሱን ይሰጣችኋል” ወይም “ትቀበሉታላችሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አንኳኩ

በር ማንኳኳት በቤቱ ውስጥ ያለው ሰው እናንተ በውጪ መቆማችሁን እንዲያውቅ ለጥቂት ጊዜ በሩን መምታት ነው። ደግሞም በባህልህ ሰዎች ወደ ቤት መድረሳቸውን ለማሳየት በሚጠቀሙበት ለምሳሌ “መጠራት” ወይም “መሳል” ወይም “ማጨብጨብ” የመሳሰሉትን መንገዶች በመጠቀም መተርጎም ይቻላል። እዚህ ጋ፣ ትርጉሙ አንድ ሰው እግዚአብሔር መልስ እስኪሰጠው ድረስ ጸሎቱን መቀጠል አለበት የሚል ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይከፈትላችኋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሩን ይከፍትላችኋል” ወይም “እግዚአብሔር ወደ ውስጥ ያስገባችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)