am_tn/luk/11/03.md

1.5 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ለደቀ መዛሙርቱ ማስተማሩን ቀጥሏል።

ስጠን … ይቅር በለን … አትምራን

እነዚህ ትዕዛዛዊ አንቀጾች ናቸው፣ ሆኖም ከትዕዛዝ ይልቅ እንደ ልመና ተደርገው መተርጎም አለባቸው። ይህንን ግልጽ ለማድረግ “እባክህን” የመሳሰለ ቃል መጨመር ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “… እባክህን ስጠን፣ እባክህን … ይቅር በለን … እባክህን አትምራን”

የዕለት እንጀራችንን

እንጀራ ውድ ያልሆነ፣ ሰዎች በየዕለቱ የሚበሉት ምግብ ነበር። እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው በጥቅሉ ምግብን ለማመልከት ነው። አ.ት፡ “በየዕለቱ የምንፈልገውን ምግብ”

ኃጢአታችንን ይቅር በለን

“በአንተ ላይ ኃጢአት ስለማድረጋችን ይቅር በለን” ወይም “የእኛን ኃጢአት ይቅር በል”

እኛ ይቅር እንደምንል

“እኛም ደግሞ ይቅር እንላለንና”

እኛን የበደለንን

“በእኛ ላይ ኃጢአት ያደረገውን” ወይም “የማይገባውን ነገር ያደረገብንን”

ወደ ፈተና አትምራን

ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከፈተና አርቀን”