am_tn/luk/10/33.md

2.2 KiB

ነገር ግን አንድ ሳምራዊ

ይህ በታሪኩ ውስጥ ስሙን ሳይጠቅስ አንድን አዲስ ሰው ያስተዋውቃል። ከሰማርያ መሆኑን ብቻ እናውቃለን። (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

አንድ ሳምራዊ

አይሁዶች ሳምራውያንን ይንቋቸው ስለነበር የቆሰለውን አይሁዳዊ ሰው አይረዳውም ብለው ገምተዋል።

እርሱ ባየው ጊዜ

“ሳምራዊው የቆሰለውን ሰው ባየው ጊዜ”

ራራለት

“አዘነለት”

ዘይትና ወይን አፍስሶባቸው ቁስሎቹን አሰረለት

በመጀመሪያ ዘይቱንና ወይኑን በቁስሎቹ ላይ ማድረግ ነበረበት። አ.ት፡ “ወይንና ዘይት በቁስሎቹ ላይ ጨምሮ በጨርቅ ጠቀለላቸው” (የሁነቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ተመልከት)

ዘይትና ወይን አፍስሶባቸው

ወይን የተጠቀመው ቁስሉን ለማጽዳት ሲሆን ዘይቱ ምናልባት ማመርቀዝን ለመከላከል ሳይሆን አይቀርም። ይህ እንደሚከተለው ሊነገር ይችላል፤ አ.ት፡ “ቁስሉ እንዲፈወስ ዘይትና ወይን በላዩ ላይ ማፍሰስ”

የራሱን እንስሳ

“የራሱ የጭነት እንስሳ”። ይህ ከባድ ጭነት እንዲሸከም የተጠቀመበት እንስሳ ነበር። ምናልባት አህያ ሳይሆን አይቀርም።

ሁለት ዲናር

“የሁለት ቀን ደሞዝ”። “ዲናር” የ”ዲናሪየስ” ብዙ ቁጥር ነው። (በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰ ገንዘብ የሚለውን ተመልከት)

አስተናጋጁ

“የሆቴሉ ጠባቂ” ወይም “የሆቴሉን ኃላፊነት የወሰደው ሰው”

የትኛውንም የምታወጣውን ተጨማሪ ወጪ ስመለስ እከፍልሃለሁ

ይህ ቅደም ተከተል እንደገና ሊስተካከል ይችላል። አ.ት፡ “በምመለስበት ጊዜ የምታወጣውን የትኛውንም ተጨማሪ ወጪ እኔ እከፍልሃለሁ”