am_tn/luk/10/23.md

1.4 KiB

ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘወር ብሎ ለብቻቸው እንዲህ አላቸው

“ለብቻቸው” የሚለው ቃል እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብቻ እንደነበረ ያመላክታል። አ.ት፡ “ከዚያ በኋላ፣ ብቻውን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በሆነ ጊዜ፣ ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አላቸው”

እናንተ የምታዩአቸውን ነገሮች የሚያዩ እነርሱ የተባረኩ ናቸው

ይህ ምናልባት ኢየሱስ ያደርጋቸው የነበሩትን መልካም ሥራዎችና ተአምራቶች ያመለክት ይሆናል። አ.ት፡ “እኔ ሳደርግ የምታዩትን ለሚያዩ ለእነዚያ እንዴት መልካም ነ

እነርሱ አላዩአቸውም

ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ እነዚያን ነገሮች ገና እንዳላደረጋቸው ነው። አ.ት፡ “ሆኖም፣ ገና ስላላደረግዃቸው ሊያዩአቸው አልቻ

እናንተ የምትሰሟቸውን ነገሮች

ይህ ምናልባት የኢየሱስን ትምህርት ያመለክት ይሆናል። አ.ት፡ “እኔ ስናገር የሰማችኋቸውን ነገሮች”

እነርሱ አልሰሟቸውም

ይህ ኢየሱስ ገና እንዳላስተማረ ያመለክታል። አ.ት፡ “ሆኖም፣ ማስተማር ባለመጀመሬ ሊሰሟቸው አልቻሉም”