am_tn/luk/10/21.md

1.9 KiB

አባት

ይህ ለእግዚአብሔር አስፈላጊ የሆነ ማዕረግ ነው። (አባት እና ልጅን መተርጎም የሚለውን ተመልከት)

የሰማይና የምድር ጌታ

“ሰማይ” እና “ምድር” ያለውን ነገር ሁሉ ይወክላል። አ.ት፡ “በሰማይና በምድር ባለው ሁሉ ላይ እና ሁሉ ነገር ላይ የበላይ”

እነዚህ ነገሮች

ይህ የሚያመለክተው ስለ ደቀ መዛሙርቱ ሥልጣን ቀደም ሲል ኢየሱስ ያስተማረውን ነው። “እነዚህ ነገሮች” በማለት ብቻ አንባቢው ትርጉሙን እንዲወስን መተው በጣም የተሻለ ሊሆን ይችላል።

ጥበበኛና አስተዋይ

“ጥበበኛ” እና “አስተዋይ” የሚሉት ቃላት ስማዊ ቅጽሎች ሲሆኑ እንዲህ ያለ ስብዕና ያላቸውን ሰዎች የሚያመለክቱ ናቸው። እነዚህ ሰዎች፣ እግዚአብሔር እውነትን ስለ ሰወረባቸው እነርሱ ነን ቢሉም እንኳን በእውነቱ ጥበበኞችና አስተዋዮች አልነበሩም። አ.ት፡ “ጥበበኞችና አስተዋዮች እንደሆኑ ከሚያስቡ ሰዎች” (ቅኔ እና ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ እንደ ትንንሽ ልጆች ያልተማሩ

ይህ የሚያመለክተው ብዙ ባይማሩም እንኳን ትንንሽ ልጆች የሚያምኗቸውን ሰዎች በፈቃዳቸው በሚሰሟቸው መልኩ የኢየሱስን ትምህርቶች ለመቀበል ፈቃደኞች የሚሆኑትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በጥቂቱ የተማሩ፣ ነገር ግን ትንንሽ ልጆች እንደሚያደርጉት እግዚአብሔርን የሚሰሙ ሰዎች”

ይህ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህ ሆኗልና

“ይህንን ማድረግ አስደስቶሃል”