am_tn/luk/10/10.md

2.9 KiB

ካልተቀበሏችሁ

“የከተማዪቱ ሰዎች ከተቃወሟችሁ”

በእግሮቻችን ላይ የተጣበቀውን የከተማችሁን አቧራ እንኳን በእናንተ ላይ እናራግፈዋለን

ይህ የከተማዪቱን ሰዎች እንደማይቀበሏቸው የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “ልክ እናንተ እንዳልተቀበላችሁን እኛም በጥንቃቄ አንቀበላችሁም። እግሮቻችን ላይ የሚጣበቀውን የከተማችሁን አቧራ እንኳን እንተውላችኋለን” (ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)

እናራግፍላችኋለን

ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች ሁለት ሁለት አድርጎ በቡድን እስከ ላካቸው ድረስ ይህንን የሚናገሩት ሁለት ሰዎች መሆን አለባቸው። ስለዚህ ሁለትነትን ገላጭ “እኛ” የሚል ቃል ያለው ቋንቋ ሊጠቀምበት ይችላል። (አግላይ እና አካታች “እኛ” የሚለውን ተመልከት)

ይህንን ግን እወቁ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርቧል

“ይህንን ግን እወቁ” የሚለው ሐረግ ማስጠንቀቂያን ያስተዋውቃል። “እናንተ ባትቀበሉንም የእግዚአብሔር መንግሥት የመቅረቡን ሐቅ አይቀይረውም!”

የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርቧል

የነገር ስም የሆነው “መንግሥት” ከግሥ ጋር “ንግሥና” ወይም “አገዛዝ” ተብሎ መገለጽ ይችላል። ተመሳሳዩን ዐረፍተ ነገር በሉቃስ 10፡8 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በቅርቡ በሁሉም ስፍራ እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ ይገዛል” ወይም “እግዚአብሔር በዙሪያችሁ ሁሉ በመግዛት ላይ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አለ” የሚሉት ናቸው (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)።

እላችኋለሁ

ኢየሱስ ይህንን ይናገራቸው የነበሩት ይልካቸው ለነበሩት ለ70ዎቹ ሰዎች ነው። ይህንን ያለው አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ሊነግራቸው እንዳለ ለማሳየት ነበር።

የፍርድ ቀን

ደቀ መዛሙርት ይህ የሚያመለክተው በኃጢአተኞች ስለሚፈረድበት የመጨረሻው ጊዜ መሆኑን ሳይረዱ አይቀሩም።

ከዚያች ከተማ ይልቅ ሰዶምን መታገስ ይቀላል

“እግዚአብሔር በዚያች ከተማ ላይ የሚፈርደውን ያህል በሰዶም ላይ አይፈርድም”። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሰዶም ሕዝብ ላይ ከሚፈርድበት በበለጠ በዚያች ከተማ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)