am_tn/luk/10/05.md

2.3 KiB

በዚህ ቤት ላይ ሰላም ይሁን

ይህ ሰላምታና ባርኮት ነበር። እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ነው። አ.ት፡ “በዚህ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሰላምን ይቀበሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሰላም ሰው

“ሰላማዊ ሰው”። ይህ ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር ሰላም እንዲኖረው የሚፈልግ ሰው ነው።

ሰላማችሁ በእርሱ ላይ ያርፍበታል

እዚህ ጋ፣ “ሰላም” የሚቆይበትን እንደሚመርጥ ሕያው ነገር ተደርጎ ተገልጿል። አ.ት፡ “የባረካችሁበት ሰላም ይኖረዋል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ካልሆነ

ሙሉዉን ሐረግ እንደገና መናገር ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “በዚያ የሰላም ሰው ከሌለ” ወይም “የቤቱ ባለቤት ሰላማዊ ሰው ካልሆነ”

ወደ እናንተ ይመለሳል

እዚህ ጋ፣ “ሰላም” ትቶ መሄድ እንደሚመርጥ ሕያው ነገር ተደርጎ ተገልጿል። አ.ት፡ “ያ ሰላም ይኖራችኋል” ወይም “የባረካችሁበትን ሰላም አይቀበልም” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በዚያው ቤት ቆዩ

ኢየሱስ በዚያ በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ አዳራቸውን በዚያው ቤት እንዲያደርጉ እንጂ ቀኑን ሙሉ እቤት ውስጥ ቆዩ ማለቱ አልነበረም። አ.ት፡ “በዚያው ቤት ማደራችሁን ቀጥሉ”

ለሠራተኛው ደሞዙ ይገባዋልና

ይህ ኢየሱስ በሚልካቸው ሰዎች ላይ ሲተገብረው የነበረ ጥቅል መርህ ነው። ሕዝቡን እስካስተማሩና እስከ ፈወሱ ድረስ ሕዝቡ ማደሪያና ምግብ ሊያቀርቡላቸው ይገባል።

ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ

ከቤት ወደ ቤት መዘዋወር ማለት ወደ ተለያዩ ቤቶች መሄድ ማለት ነው። እርሱ ይናገር የነበረው በተለያየ ቤት ስለ ማደር መሆኑን ግልጽ ማድረግ ይቻላል። “በየምሽቱ በተለያየ ቤት አትደሩ”