am_tn/luk/10/03.md

1.2 KiB

መንገዳችሁን ሂዱ

“ወደ ከተሞቹ ሂዱ” ወይም “ወደ ሕዝቡ ሂዱ”

እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ

ተኩላዎች በጎችን ያጠቃሉ፣ ይገድላሉም። በመሆኑም የዚህ ዘይቤአዊ አነጋገር ትርጉም ኢየሱስ በሚልካቸው ደቀ መዛሙርት ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚሞክሩ ሰዎች ይኖራሉ የሚል ነው። የሌላ የዱር አውሬ ስም ሊተካ ይችላል። አ.ት፡ “በምልካችሁ ጊዜ ተኩላዎች በጎችን እንደሚያጠቁ ሰዎች ሊጎዱአችሁ ይፈልጋሉ”

የገንዘብ መያዣ ወይም የመንገደኛ ሻንጣ ወይም ጫማ አትሸከሙ

“ቦርሳ፣ የመንገደኛ ሻንጣ፣ ወይም ጫማ ከእናንተ ጋር አትውሰዱ”

በመንገድ ላይ ለማንም ሰላምታ አትስጡ

“በመንገድ ላይ ማንንም ሰላም አትበሉ”። ኢየሱስ በፍጥነት ወደ መንደሮች እንዲሄዱና ይህንን ሥራ እንዲሠሩ አጽንዖት እየሰጠ ነበር። እርሱ ባለጌ እንዲሆኑ እየነገራቸው አልነበረም።