am_tn/luk/10/01.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢየሱስ ተጨማሪ 70 ሰዎችን በፊቱ አስቀድሞ ይልካቸዋል። እነዚያ 70ዎቹ በደስታ ይመለሳሉ፣ ኢየሱስም ለሰማይ አባቱ የምስጋናን ምላሽ ያቀርባል።

በዚህ ጊዜ

እዚህ ጋ ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በታሪኩ ውስጥ አዲስ ሁነትን ለማመልከት ነው። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

ሰባ

“70”። አንዳንድ ትርጉሞች “ሰባ ሁለት” ወይም “72” ይላሉ። ይህንን የሚናገር የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ያስፈልግህ ይሆናል። (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)

ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው

“ሁለት ሰዎችን የያዘ ቡድን አድርጎ ላካቸው” ወይም “በእያንዳንዱ ቡድን ሁለት ሰዎችን አድርጎ ላካቸው”

እንዲህ አላቸው

በእውነቱ ይህ የተነገረው ሰዎቹ ከመሄዳቸው በፊት ነው። አ.ት፡ “እንዲህ ብሏቸው ነበር” ወይም “ከመሄዳቸው በፊት ነገራቸው” (የሁነቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ተመልከት)

መከሩ ብዙ ነው፣ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው

“ሰብሉ ብዙ ነው፣ የሚያስገቡት ሠራተኞች ግን በቂዎች አይደሉም”። ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የተዘጋጁ ሰዎች ብዙዎች ናቸው፣ ሕዝቡን ለማስተማርና ለመርዳት የሚሄዱ ደቀ መዛሙርት ግን በቂዎች አይደሉም” ማለቱ ነበር። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)